ኤመራልድ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን ሴት አመራሮች አስመረቀ

ኤመራልድ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን ሴት አመራሮች አስመረቀ

8 September 2025 | Emerald Team

ኤመራልድ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን ሴት አመራሮች አስመረቀ!

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ከኤመራልድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ጋር በጋራ በመሆን ሴቶች በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው እና በማህበራዊ ዘርፍ ያላቸውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ በማለም በአመራር ሁለተኛ ዲግሪ 'MA in Leadership' ነፃ የትምህርት ዕድል ከ18 ሚኒስትር መስርያ ቤት ለተመረጡ ከፍተኛ እና መካከለኛ ሴት አመራሮች በመስጠት ትምህርታቸውን ስከታተሉ ቆይተዋል።

በመሆኑም በዓይነቱ እና በይዘቱ ልዩ የሆነውን ለሀገራችን ሴቶች ዘርፈብዙ ትርጉም የሚሰጠውን የሴት አመራሮች የሁለተኛ ዲግሪ ምርቃት ፕሮግራም ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በተገኙበት በሂልተን ሆቴል ጳጉሜ 2/2017 ተካሄዷል።

በዚህ ደማቅ የምርቃት ፕሮግራም ላይ በመገኘት ለተመራቂዎቹ መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን የትምህርት ተቋማት በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሴቶች ቁጥር ከፍ አንዲል  የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አደራ ብለዋል።

የሴቶች ጉዳይ ሁሉንም ማህበረሰብ እና ተቋማት የሚመለከት መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን መንግሥት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚሰራቸው ዘርፈብዙ ስራዎች በተጨማሪ የባለድርሻ አካላት የሚያከናውኑት ተግባር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ትምህርት ሀገር ያበለጽጋል ትምህርት የእድገት ሞተር ነው ተመራቂዎች በጽናታችሁ ያገኛችሁትን ታላቅ ስጦታ ሀገራችሁን ቀይሩበት ወደ ተግባርም ቀይሩት ብለዋል።

ያልተማረና ያልተመራመረ ሰው የትም አይደርስም እራሱም ሆነ ሀገርም መለወጥ የሚቻለው በትምህርት ብቻ መሆኑ መታወቅ አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አሁን የምንገኝበት የዲጅታል ዘመን በርካታ እድሎችና ፈተናዎች ያሉበት ነው ብለው በዲጂታል ዘመን ያገኛችሁትን እድል በአግባቡ ተጠቀሙበት ብለዋል። ኢትዮጵያ የዲጂታል ዘመን መሰረት ያደረገ  ስራ እየሰራች ትገኛለች ያሉት ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ኤምራልድ ኮሌጅ ይህንን በተግባር አሳይቷል ሲሉ ነው የገለፁት።

ዶ/ር ተስፋዬ ለተመራቂዎች ቢያስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ከእናንተ ብዙ ትጠብቃለች በማለት የተማራችሁትን ወደ ተግባር ቀይራችሁ እራሳችሁና ሀገራችሁን መለወጥ መቻል አለባችሁ ብለዋል።

በምረቃ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግዳነት የተገኙት በትምህርት ሚኒስትር የአስተዳደና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ የኢትዮጵያ መንግስት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አስተዳደርን፣ ትምህርትን፣ ግብርናን፣ ጤናን እና ኢንዱስትሪን በዲጂታል መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ኃይል ለመቀየር መንግሥት ሀገራዊ አጀንዳ አድርጎ መተግበር ከጀመር ዓመታትን አስቆጥሯል ብለዋል።

የኤመራልድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ፕሬዘዳንት የሆኑት ዶ/ር አደም ኢብራሂም በምረቃ ተቋማቸው ኤመራልድ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ የትምህርት፣ የምርምርና የአቅም ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ስሉ ተናግረዋል።

ኤመራልድ ኢትንተርናሽናል ኮሌጅ ከተቋቋመ አራት አመት ያስቆጠረ ሲሆን በዳታ ሳይንስ እንዲያሰለጥን ከትምህርት ሚኒስትር እውቅና የሰጠው ብቸኛ ተቋም ነው።

Contact

map-icon

Lideta next to tesfa kokeb school, Addis Ababa, Ethiopia

mail-icon

info@emerald.edu.et

phone-icon

+251 (907) 111-177/99

Admissions

2025 © Emerald International College