8 September 2025 | Emerald Team
#Ethiopia | ኤመራልድ በኢትጵያ የመጀመሪያ የሆነውን በዳታ ሳይንስ የግል የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር በማስጀመር ታሪክ ሰርቷል!
ጳጉሜ 02/2017 | ኤመራልድ ኢንትርናሽናል ኮሌጅ በሶስት የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መርሀግብሮች ያስተማራቸውን 184 ተማሪዎች ከፍተኛ የመንግሥት አካላት በተገኙበት በሂልተን ሆቴል አስመረቀ።
በአመራር የትምህርት ዘርፍ፣ በዳታ ሳይንስና በኤምቢ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን ነው ያስመረቀው።
ኤመራልድ ኢትንተርናሽናል ኮሌጅ ከተቋቋመ አራት አመት ያስቆጠረ ሲሆን በዳታ ሳይንስ እንዲያሰለጥን ከትምህርት ሚኒስትር እውቅና የሰጠው ብቸኛ ተቋም ነው።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን የትምህርት ተቋማት በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሴቶች ቁጥር ከፍ አንዲል የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አደራ ብለዋል።
የሴቶች ጉዳይ ሁሉንም ማህበረሰብ እና ተቋማት የሚመለከት መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን መንግሥት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚሰራቸው ዘርፈብዙ ስራዎች በተጨማሪ የባለድርሻ አካላት የሚያከናውኑት ተግባር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ትምህርት ሀገር ያበለጽጋል ትምህርት የእድገት ሞተር ነው ተመራቂዎች በጽናታችሁ ያገኛችሁትን ታላቅ ስጦታ ሀገራችሁን ቀይሩበት ወደ ተግባርም ቀይሩት ብለዋል።
ያልተማረና ያልተመራመረ ሰው የትም አይደርስም እራሱም ሆነ ሀገርም መለወጥ የሚቻለው በትምህርት ብቻ መሆኑ መታወቅ አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አሁን የምንገኝበት የዲጅታል ዘመን በርካታ እድሎችና ፈተናዎች ያሉበት ነው ብለው በዲጂታል ዘመን ያገኛችሁትን እድል በአግባቡ ተጠቀሙበት ብለዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል ዘመን መሰረት ያደረገ ስራ እየሰራች ትገኛለች ያሉት ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ኤምራልድ ኮሌጅ ይህንን በተግባር አሳይቷል ሲሉ ነው የገለፁት።
ዶ/ር ተስፋዬ ለተመራቂዎች ቢያስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ከእናንተ ብዙ ትጠብቃለች በማለት የተማራችሁትን ወደ ተግባር ቀይራችሁ እራሳችሁና ሀገራችሁን መለወጥ መቻል አለባችሁ ብለዋል።
በምረቃ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግዳነት የተገኙት በትምህርት ሚኒስትር የአስተዳደና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ
የኢትዮጵያ መንግስት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አስተዳደርን፣ ትምህርትን፣ ግብርናን፣ ጤናን እና ኢንዱስትሪን በዲጂታል መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች ኃይል ለመቀየር መንግሥት ሀገራዊ አጀንዳ አድርጎ መተግበር ከጀመር ዓመታትን አስቆጥሯል ብለዋል።
ዶ/ር ሰለሞን አክለውም ስትራቴጂው በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነት ኢኮኖሚያችንንና ህብረተሰባችንን ለመለወጥ እየተደረገ ያለውን ስራ በአግባቡ እየመራ ነው ስሉ ገልፀዋል።
በመላ አገሪቱ አምስት ሚልዮን ኮድ አውጪዎችን ለማሠልጠን በመንግሥት በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በመሠራት ላይ መሆኑን የተነጋገሩት ዶ/ር ስለሞን ወጣቶቻችንን ኮድ በማውጣት ችሎታ እና በዲጂታል እዉቀት በማስታጠቅ፣ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያረጋግጡ እና የስራ እድል የሚፈጥሩ አዲስ የፈጠራ ትውልድ መፍጠር እንደምንችል የታየው ወጤት አመላካች ነው ብለዋል።
ኤመራልድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን በዳታ ሳይንስ የግል የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር በማስጀመር ታሪክ ሰርቷል ያሉት የዕለቱ የክብር እንግዶች፤ ለዚህም ሊመሰገን እና ሊበረታታ፤ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
በዳታ ሳይንስ እውቅና አግኝቶ ለመጀመርያ ጊዜ ተማሪዎቹን ያስመረቀው ኤመራልድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ባመቻቸው የነጻ የትምህርት እድል ከ18 የመንግስት መስራቤት የመጡ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች በአመራር የትምህርት ዘርፍ አስመርቋቸዋል። ዛሬ ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል 57ቱ ሴት ተመራቂዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወንድ ተመራቂዎች ናቸው።
ኤመራልድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ የመማር ማስተማር ስራውን ከጀመረ ገና አራት አመታት ቢሆነውም በተሰጠው እውቅና በሶስት የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎቹን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።